የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 12/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ “ህዳር ሲጸዳ” በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማችን ደረጃ በወረዳ10 የፅዳት ንቅናቄ ይካሄዳል። በፅዳት ንቅናቄ ስራውም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የጽዳት መርሃ ግብር ዘረኝነትን፣እርስ በእርስ መገፋፋትንና ጥላቻን ጠራርገን በመጣል በምትኩ ፍቅርን፣አንድነትንና አብሮነትን የምንተክልበት መርሃ ግብር ነው፡፡ በእዚህ ንቅናቄ ላይ የከተማችን ምክትል ከንቲባን ጨምሮ የከተማችን አመራሮች የሚገኙ ሲሆን ህግን በማስከበር ጁንታውን የህወሐት ቡድን ለመደምሰስና የትግራይንና የኢትዮጵያን ህዝቦች ነጻ ለማውጣት በብርቱ እየተጋ የሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንም የሚታሰብ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በክፍለ ከተማችን በተከናወነው የሀብት አሰባሰብ የተገኙ ከ80 በላይ በሬዎች በወረዳ 7 ለመከላከያ ሰራዊታችን የሚበረከቱ ይሆናል፡፡
ስለሆነም የክፍለ ከተማችን እና የወረዳ አመራሮች ሰራተኛውንና ህዝቡን በማሳተፍ የጽዳት ዘመቻው በደመቀ መልኩ እንዲከናወን ከወዲሁ የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት እንድናደርግ በነገው እለትም መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ የንቅናቄው ተሳታፊ እንዲሆንና ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጎን እንዲቆም የተጠናከረ ስራ እንዲሰራ አሳስባለሁ!! በፅዳት ንቅናቄው ላይ የተሰበሰበውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በመያዝ እና በአይነቱ በመለየት በአካባቢያችን ለተመደቡ የህብረት ሽርክና ፅዳት ማህበራት እናስረክብ።
አካባቢያችንን ከቆሻሻ ውስጣችንን ከዘረኝነት፣ጥላቻና ተንኮል እናጽዳ!!