‹‹ህገ ወጥነትን መጋፈጥ ህጋዊነትን ለማስፈን ቁልፍ ጉዳይ ነው!››

‹‹ህገ ወጥነትን መጋፈጥ ህጋዊነትን ለማስፈን ቁልፍ ጉዳይ ነው!››

  • Post author:
  • Post category:ልዩ ልዩ
  • Post last modified:February 19, 2021
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:0 mins read

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የብልጽግና አመራር በህገ ወጥነት ላይ በመዝመት ህጋዊነትን ለማስፈን ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ አመራር ህገ ወጥነትን ፊት ለፊት ሲጋፈጥ ህገ ወጦች እንደማያመሰግኑት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ አመራሩ ህገ ወጥነትን የሚጋፈጠው ክፍለ ከተማው ህግ የበላይነት የተረጋገጠበት እንዲሆን ካለው ጽኑ ፍላጎት እንደሆነ ማስገንዘብ ይፈልጋል፡፡ እንደ ብልጽግና አመራር የህገ ወጦችን ምሽግ ለማፈራረስ ቆርጠን ወደ ተግባር ስንገባ ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ ህገ ወጦች እንደማይደሰቱ ነገር ግን ህጋዊ ስርዓት እንዲሰፍን የሚሹ በርካቶች እንደሚደግፉን ስለምንገነዘብ ነው፡፡

መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ህገ ወጥነትን እንድንታገል በተለያዩ መድረኮች ደጋግሞ ጠይቆናል አቤቱታውንም አሰምቷል፡፡ ወደ ተግባር ከገባንባት የመጀመሪያዋ እለት አንስቶም ከጎናችን በመሆን ጥቆማ ሰጥቶናል በተግባርም አግዞናል፡፡ ይህ የህብረተሰባችን ድጋፍ በህገ ወጦች ላይ እየወሰድን ለምንገኘው እርምጃ ብርታትና ወኔ ሆኖናል፡፡ የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ጥቅም ሊረጋገጥ የሚችለው ህገ ወጥነት ተወግዶ በምትኩ ህጋዊነት ሲሰፍን ነው፡፡ ነዋሪያችን በህገወጦችና የእነሱ ጀሌዎች ደባ ላለፉት ጥቂት የማይባሉ አመታት የበይ ተመልካች ሆኖ ቆይቷል፤ተበዝብዟል፤ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችም ተዳርጓል፡፡ እኛም በህገ ወጥነት ላይ በመድረክ ስንፎክርና ስንዝት ጊዜ ገዝተን ስርዓት አልበኝነት አእንዲነግስ ዕድል ፈጥረን ቆይተናል፡፡

ዛሬ ግን ለዘመናት መረቡን ዘርግቶ የቆየውን የህገ ወጥነት የእላፊ ተጠቃሚነትና የአልጠግብ ባይነት ሰንሰለት ከነዋሪዎቻችን ጋር ተቀናጅተን ለመበጣጠስ ቆርጠን ተነስተናል፡፡ ውጤቶችንም እያስመዘገብን እንገኛለን፡፡ በመሆኑም ማንም ተደሰተ ማንም ተከፋ በህገ ወጥነት ላይ የጀመርነውን ዘመቻ ለአፍታም አናቆምም፡፡ በእዚህ ሂደት ውስጥ እየገጠሙን ያሉ ተግዳሮቶች ቀላል አለመሆናቸውን የክፍለ ከተማችን ነዋሪ እንዲገነዘብልንና የጀመረውን ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ከጎናችንም እንዲቆም እንሻለን፡፡

ኮልፌ ቀራኒዮ ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ

Leave a Reply