‹‹ህገ ወጥነት የብልጽግናችን ሰንኮፍ በመሆኑ እንንቀለው!!››

‹‹ህገ ወጥነት የብልጽግናችን ሰንኮፍ በመሆኑ እንንቀለው!!››

  • Post author:
  • Post category:ዜና
  • Post last modified:February 19, 2021
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:0 mins read

ብልጽግና የሀገራችን ህዝቦች የመዳረሻ ምዕራፍ እንዲሆን በፓርቲያችን አመራሮች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥና የእለተ እለት ህይወቱን በመቀየር ረገድ እየተከፈሉ ያሉ መስዋእተነቶች ለመዳረሻው ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ብልጽግናችንን የሚገዳደሩ ሰንኮፎች እዚህም እዚም ብቅ ብቅ ማለታቸው አሁንም ቢሆን አልቀረም፡፡ እንደ ክፍለ ከተማችንም ከእነዚህ ሰንኮፎች መካከል አንዱ የሆነው ህገ ወጥነት ባለ መልከ ብዙ ሆኖ ከጀመርነው አገራዊ ጉዞ ሊያደናቅፈን እየታገለን ይገኛል፡፡ አመራራችንና የክፍለ ከተማችን ነዋሪም ይህን ሰንኮፍ በመንቀል ብልጽግናን ለማረጋገት በጋራ እየዘመተ ውጤትም እየተገኘ ነው፡፡ የህዝብን ምሬት የሚጨምሩና በጉሮሮው ላይ የሚቆሙ ህገ ወጥነቶችንም ተከታትሎ አደብ በማስያዝ ላይ ይገኛል፡፡ በክፍለ ከተማችን ወረዳ 12 በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 6ሺህ 600 ካርቶን (132ሺህ ሊትር) የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። ለክፍለ ከተማችን ነዋሪዎችና የየፀጥታ ሀይሎች ከአመራሮቻችን ጋር በመቀናጀት ህገወጦችን ለማጋለጥ ላደረጋችሁት  ክትትልና ቁጥጥር የሚመሠገን ሲሆን በህገወጥ ተግባራት ላይ የተሰማሩ አካላትን የማጋለጡ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር እንደሆነም ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡

Leave a Reply