“አብሮነትና ወንድማማችነት ጎልቶ የታየበት የጽዳት ዘመቻ”

“አብሮነትና ወንድማማችነት ጎልቶ የታየበት የጽዳት ዘመቻ”

  • Post author:
  • Post category:ዜና
  • Post last modified:January 24, 2021
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:1 mins read
በአገራችን በኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ዘንድ የዓመቱ በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 በሚገኘው የታቦት ማደሪያ አብሮነትና ወንድማማችነት ጎልቶ የታየበት የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል። በእዚህ ንቅናቄ ላይ ከዕምነቱ ተከታዮች ባሻገር የእስልምና እምነትና የሌሎችም እምነት ተከታዮች ተገኝተው አብሮነታቸውን አሳይተዋል።
ይህ ድንቅ አብሮነትና አንድነት ኢትዮጵያን በኃይማኖት ለመከፋፈል ለሚሹ የጥፋት ኃይሎች እንደማይሳካላቸው መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑን በጽዳት መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙቀት ታረቀኝ ተናግረዋል።

ስራ አስፈጻሚው፤ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያውያን እርስ በእርሳቸው እንዲጠራጠሩና እንዳይተማመኑ ብሎም ለዘመናት ይዘውት የተሻገሩትን የአንድነትና የአብሮነት እሴት ለመናድ በብሔርና በኃይማኖት ለመከፋፈል በርካታ ሴራዎች መጎንጎናቸውን አንስተዋል። 

ይሁን እንጂ ይህን መርዝ የረጩት የጥፋት ኃይሎች ህልማቸውና ውጥናቸው ቅዠት ሆኖ ለአገራችንና ለህዝቦቿ መቀበርያ አርቀው በቆፈሩት ጉድጓድ እነሱ ገብተውበታል ብለዋል።
በጥምቀተ ባህሩ ከ13 በላይ ታቦታት በጋራ እንደሚያድሩ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply