‹‹ወቅቱ በርካታ ችግሮችን የምንዘረዝርበት ሳይሆን አንዲት ፍሬ መፍትሔ የምናበረክትበት ይሁን!››

‹‹ወቅቱ በርካታ ችግሮችን የምንዘረዝርበት ሳይሆን አንዲት ፍሬ መፍትሔ የምናበረክትበት ይሁን!››

  • Post author:
  • Post category:ዜና
  • Post last modified:January 13, 2021
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:1 mins read

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙቀት ታረቀኝስራ አስፈጻሚው ይህ ያሉት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከወረዳ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረውን የ2013 ዓ.ም የመንግስትና የድርጅት መሪ ዕቅድ ውይይት ባጠቃለሉበት ወቅት ነው፡፡

የውይይት መድረኩ መድረክ በትናንትናው እለት በክፍለ ከተማ ደረጃ በተካሄደበት ወቅት የማጠቃለያ መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ስራ አስፈጻሚው አቶ ሙቀት ታረቀኝ በእዚህ ፈታኝና ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚታገሉ ኃይሎች ጋር እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ በሚደረግበት፤ዘራፊውና አፋኙ የትህነግ/ህወሀት ቡድን ላይመለስ ወደ መቃብር በወረደበት ወቅት በብልጽግና ጥላ ስር ‹አመራርነት ለመስጠት እድሉን በማግኘታችን ልንኮራ ይገባል‹ ብለዋል፡፡

አመራሩ ይህን በታሪክ ውስጥ የመዘከር መልካም እድል በመጠቀምም ለብልጽግና ጉዟችንና ለለውጡ ከግብ መድረስ ወሳኝ የሆኑ ተግባራትን ለመፈጸም ቆሮጦ በመነሳት ከልብ የመነጨና እውነተኛ አገልግሎት በመስጠት የህዝቡን እንግልት ለመቅረፍ መስራት እንዳለበትም አቶ ሙቀት አመላክተዋል፡፡ 

የአመራር ዲሲፕሊን የተግባራችን ሁሉ አልፋና ኦሜጋ መሆን አለበት ያሉት ስራ አስፈጻሚው፤አመራሩ ለህዝብ እራሱን የሰጠ፤ኃላፊነት የሚሰማው፤ቅንና አርአያ መሆን የሚችል፤ስርቆትን የሚጸየፍና ከብልሹ አሰራሮች እራሱን ያቀበ ሊሆን እንደሚገባም አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

የምንመራው ስልጡኑን፤የተማረውንና ለቴክኖሎጂ ስልጣኔ ቅርብ የሆነውን የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በመሆኑ እንደተራ አመራር እራሳችንን ማየት የለብንም ሲሉ አውስተዋል፡፡ ስራ አስፈጻሚው ከታች እስከላይ የሚገኘው ሁሉም አመራር ይህን ሊመጥን የሚችል የአመራር ሰጪነት ሚናውን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

Leave a Reply