በክ/ከተማችን ወጣቶች ብሔራዊ አንድነታቸውን ጠብቀው የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል ማጎልበት በሀገራዊ ጉዳዮች ገንቢ ሚና እንድጫወቱ መስራት፡፡
በፓርቲዉና በወጣቱ መሃል መሸጋገሪያ ድልድይ በመሆን ቀጣይ ሃገር ተረካቢ ወጣት ትውልድ መፍጠር የብልፅግና አላማ እና ህልውና በቀጣይነት ማረጋገጥ፡፡
በክ/ከተማችን ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ በብልፅግና አላማዎች ዙሪያ የተሰባሰቡ ወጣቶች የመታገያ መድረክ ሆኖ ማገልገል፡፡
- የብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራም በህዝቡ ውስጥ ሰርፆ ጠንካራ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ቅቡልነት ያለው፣ ዘላቂ ሀገረ መንግሥት ግንባታ በስራ እንድተረጎም እና በዘላቂነት የወጣቶች ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ መስራት፡፡
- በክ/ከተማችንን ወጣቶች ሁለንተናዊ ብልፅግናን የሚያሰፍን ማኅበራዊ ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል እና የብልፅግና አላማዎችን ለማሳካት መታገል፡፡
- በክ/ከተማችን ወጣቶች በአስተሳሰብና በተግባር አለም ከደረሰበት የፖለቲካ ኢኮኖሚ ብልፅግና ደረጃ ላይ እንዲደርሱ መስራት፡፡