‹‹የኢትዮጵያውያን ሀብት የአፍሪካውያን ኩራት አድዋ!››

‹‹የኢትዮጵያውያን ሀብት የአፍሪካውያን ኩራት አድዋ!››

  • Post author:
  • Post category:ዜና
  • Post last modified:February 19, 2021
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:0 mins read

ኢትዮጵያውያን ኩሩ ህዝቦች ናቸው ሲባል በበርካታ ምክንያቶች ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ላቅ ብሎ የሚወሳውና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣው የኩራት ምንጭ ግን አድዋ ነው፡፡ የአይበገሬነትና የአልደፈር ባይነት ወኔና ጀግንነት የተንጸባረቀበት ታሪክ፡፡ አድዋ አንድነት፤አብሮነት፣ወንድማማችነትና ሉዓላዊነት ከፍ ብሎ የታየበት ዓውደ ጀግነነት በመሆኑ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ቦታ አለው፡፡

የትናት አባቶቻችን በቴክኖሎጂ ጠንካራ ከሆነችው ጣሊያን ጋር በባህላዊ የጦር መሳሪያ ተዋግተው ያሸነፉትና ድል አድራጊነትንና ኩራትን ያወረሱን ለአገራቸው ከነበራቸው ልዩ ፍቅርና ክብር በመነሳት ነው፡፡ በወቅቱ በቅኝ ግዛት ውስጥ የነበሩትና ይህን የጀግኖች ኢትዮጵያውያንን አልቀመስ ባይነት የተመለከቱ በርካታ የአፍሪካ አገራት ዓድዋን የትግላቸውና የነጻነት መውጫቸው አብነት አድርገው መውሰድ ችለዋል፡፡

ዓድዋ ዛሬ እራስን ከድህነት በማላቀቅ ወደ ብልጽግና መሸጋገር ነው፡፡ ዓድዋ ዛሬ አገራዊ አንድነትን፤ወንድማማችነትንና አበብሮነትን ማጎልበት ነው፡፡ ዓድዋ ዛሬ ከጽንፈኝነት፤ከጎጠኝነት በመላቀቅ ለአገራዊ እሴቶችና ህብረ ብሔራዊ አንድነት እራስን አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ በእዚህ ዘመን ከእዚህ ውጪ አድዋ የለም፡፡

 ኮልፌ ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ

Leave a Reply