‹‹የይቻላል መንፈስን በመላበስ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን እንቅረፍ››

‹‹የይቻላል መንፈስን በመላበስ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን እንቅረፍ››

  • Post author:
  • Post category:ዜና
  • Post last modified:February 19, 2021
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:0 mins read

የይቻላል መንፈስና ወኔን መላበስ የህብረተሰቡ የቅሬታ ምንጭ ለሆነው  አገልግሎት አሰጣጥ ፍቱን መድኃኒት መሆኑን የተናገሩት ስራ አስፈጻሚው፤  አመራሩ ቁርጠኛ መሆንና ችግሩን መፍታት እችላለሁ የሚል እሳቤን በውስጡ ይዞ መንቀሳቀስ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡ ደቡብ ኮርያ ከማህበረሰብ አገልግሎት አሰጣጥ አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመርያውን ረድፍ የያዘች ሀገር መሆኗን ያወሱት አቶ ሙቀት ይህ ተሞክሮ ቤታችን ድረስ መጥቶ ማግኘታችን እኛም እነሱ የረገጡትን ድንጋይ ረግጠን ወደተሻለ ደረጃ እንድናድግ ብሎም የአገልግሎት አሰጣጣችንን ፍትሃዊ፤ቀልጣፋና ለሁሉም በሁሉም ስፍራ ተደራሽ ለማድረግ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠትም እራስን ለተገልጋዩ መስጠት፤ከማንኛውም አይነት እጅ መንሻ ማቀብና የአገልግሎት ማእከልን የህዝብ እርካታ ብቻ ማድረግ ተገቢ መሆኑንም አቶ ሙቀት ጠቁመዋል፡፡

Leave a Reply