‹‹የፓርቲና የመንግስት ስራዎቻችን በጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ይታጀቡ!››

‹‹የፓርቲና የመንግስት ስራዎቻችን በጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ይታጀቡ!››

  • Post author:
  • Post category:ዜና
  • Post last modified:January 13, 2021
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:0 mins read

እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ መንግስት ከአመት እስከ አመት ድረስ የህዝብን ተጠቃሚነት ማዕከል አድርገን የምናከናውናቸው ተግባራትን ለምንሰራለት ህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ያለብን ችግር የትየለሌ ነው፡፡ አንዳንዶች ጥቂት ሰርተው ብዙ ሲያወሩ እኛ ግን ‹‹ከብዙ ወሬ ጥቂት ስራ›› በሚል ያፈጀ አባባል ተሸብበን ብዙ ስራችንን ሳናስተዋውቅ ያለፉን ዘመናት ሊቆጩን ይገባል፡፡ በእርግጥ አሁን እንግባበት እያልን ያለነው የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ስራችን ‹ጤፍ ያለው ያግባሽ ወይንስ አፍ ያለው› አይነት ተረት እንዳይሆንብን መጠንቀቅ የግድ ይለናል፡፡ የህዝብ ግንኙነት ስራችን ዋናው ቁም ነገሩ የየእለቱ ልፋትና ድካማችን በምን ምክንያት፤ለምንና ለማን እንደሆነ ማሳወቅና ህዝቡን የተግባራቱ ባለቤት በማድረግ ከጠያቂነት ወደ ዋና ተዋናይነት ማሸጋገርና የአጋዥነት ሚናውን እንዲወጣ ማድረግ ነው፡፡ በእዚህ ውስጥ የእኛ ትርፍ የሚሆነው የህዝባችንን ቀልብ በመሳብ የፓርቲያችንንና በእርሱ የሚመራውን መንግስት ቅቡልነት ማረጋገጥ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡

መላው በየደረጃው የምትገኙ የፓርቲያችን አመራሮቻች ዘመኑ የግሎባለይዜሽን ነውና እያንዳንዱ ልፋትና ድካማችሁን ለምትመሩት ህዝብ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ማስተዋወቅን አትዘንጉ፡፡ መልካም አፈጻጸሞቻችሁን በመቀመር ከምትመሩት ህዝብ አይንና ጆሮ አድርሱ፡፡ ደከም ያለባችሁን አፈጻጸም ደግሞ ለማሻሻል ቁርጠኛ ስለመሆናችሁ ህዝባችሁ ይወቅ፡፡ በየትኛውም አጋጣሚና ቦታ ሁሉ ለመረጃ ቅርብና ቀዳሚ፤ ተደራሽና ፈጣን መልስ ሰጪ ሁኑ፡፡ ውጤታችሁን በምትመሩበት ስፍራና ቦታ ብቻ ሳትወስኑ ዓለምን እንዲደርስ ትጉ!!

Leave a Reply