‹‹ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለብልጽግና ጉዟችን ስኬት እናውለው!››

‹‹ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለብልጽግና ጉዟችን ስኬት እናውለው!››

  • Post author:
  • Post category:ዜና
  • Post last modified:January 13, 2021
  • Post comments:1 Comment
  • Reading time:1 mins read

ብዝሃነታችን የምንዋብበት፣ የምንደምቅበትና ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጉልተን  የምናሳይበት ጌጣችን ነው፡፡ ህብረ ብሔራዊነታችን ደግሞ እኛ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርሳችን እንድንተዋወቅ፣ ትስስራችንን እንድናጠናክር ከማድረጉም ባሻገር በዓለም አደባባይም ጎልተን እንድንታይ ካደረገን መገለጫችን መካከልም ነው። እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በአብሮነት ቆይታችን ዘመን የጋራ እሴቶቻችን ያዳበርን ከመሆናችንም በላይ በመተማመንና በመተባበር አገር ያቆምን አገራችንን ከጠላት ለመከላከል በጋራ የተሰለፍን፣ የተዋደቅንና የተሰዋን ህዝቦችም ነን፡፡

ይህን በህብረ ብሔራዊ አንድነታን መነሾ ያገኘነውን ድል የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ሂደት ሰላምን በማረጋገጥ፣ መልካም አስተዳደርን በማስፈን፤ ፈጣንና ሁለንተናዊነት ያለውን ልማት በማረጋገጥ ረገድ የበለጠ አቅም በሚፈጥር መልኩ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ በመሆኑም ህዝቦች የግላችን በሚሉት ማንነታቸው ሊኮሩ እና የጋራ በሆነው ኢትዮጵያዊ ማንነታቸው በህብር እንዲቆሙ በመከባበር፣ በወንድማማችነትና በመተማመን ላይ የተመሰረ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር ለነገ የማይባል የቤት ስራችን መሆኑን ልንገነዘብ ያስፈልጋል። እንደ አገር ለመቀጠልና የብልጽግና ጉዟችንን ከዳር ለማድረስ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ጠብቀን ከመጓዝ ውጪ አማራጭ እንደሌለን መረዳት ያሻል፡፡ ትናንት ወደነበርንበት የብሔር ዋሻ ተመልሰን አንዳችን ሌላችንን እየተጠራጠርን የምንኖርበት ጊዜ ዳግም ላይመለስ አክትሞለታል፡፡ እርስ በእርስ ከመደጋገፍና አብሮ ከመቆም ውጪ ኢትዮጵን ሊያሻግር የሚችል ምንም አይነት መፍትሔ አለመኖሩንም ጠንቅቀን መረዳት ለተግባራዊነቱም መረባረብ አለብን፡፡

This Post Has One Comment

  1. Hi, this is a comment.
    To get started with moderating, editing, and deleting comments, please visit the Comments screen in the dashboard.
    Commenter avatars come from Gravatar.

Leave a Reply